በርሊን፤ የከባቢ አየር ጥበቃ ትኩረት እንዲያገኝ የተጠራ ተቃውሞ
ቅዳሜ፣ መስከረም 24 2012ማስታወቂያ
የከባቢ አየር ለውጥ ትኩረት እንዲያገኝ የሚወተውቱ አራማጆች በበርሊን ከተማ ከመራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ፅህፈት ቤት ደጃፍ መጠለያ መገንባት ጀመሩ። አራማጆቹ በሚቀጥለው ሳምንት ለከባቢ አየር ለውጥ መፍትሔ የሚያበጁ ፖሊሲዎች እንዲዘጋጁ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሔድ አቅደዋል። የሰልፉ አደራጅ አኔማሪየ ቦትዝኪ እንዳሉት መንግሥት በባለሙያዎች ሐሳብ ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ እንዲያዘጋጅ በሚጠይቀው ተቃውሞ ከመላው ጀርመን የተውጣጡ ከ 5,000 በላይ ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። የጀርመን መንግሥት በቅርቡ ያዘጋጀው ምክረ ሐሳብም ሆነ ከዚህ ቀደም ሥራ ላይ የነበረው ፖሊሲ በቂ አይደለም ሲሉ ቦትዝኪ ተችተዋል። ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ የበርሊን ከተማ ዋና ዋና መንገዶችን ይዘጋል ተብሎ ይጠበቃል።
እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ