በህዳሴ ግድብ ምርቃት ሰሞን የሚደረገው የኢትዮጵያ እና ግብጽ የእግር ኳስ ግጥሚያ እና ሌሎች
ሰኞ፣ ነሐሴ 19 2017የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ቀሪ የማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት እያደረገ ነው። ካይሮ ላይ ከግብጽ ብሔራዊ ቡድን ጋር ለሚያደርገው ተጠባቂ ጨዋታ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድኑ ያለበትን አቋም እንጠይቃለን። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በብራሰልስ የዳይመንድ ሊግ ውድድር በተወዳደሩባቸው የተለያዩ ርቀቶች ማሸነፍ አልቻሉም ። በሁለት ውድድሮች 2ኛ ደረጃ ያገኙባቸው ውጤቶች ከፍተኛው መሆኑ ተሰምቷል ። የጀርመን ቡንደስ ሊጋ አዲሱ የውድድር ዓመት በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በይፋ ተጀመሯል። ። ሻምፒዮኑ ባየር ሙንሽን እና አይንትራ ፍራንክፈርት ተጋጣሚዎቻቸውን በሰፊ የጎል ልዩነት ባሸነፉበት የመክፈቻ ጨዋታዎች ባየር ሊፈርጉሰን እና ቦሩሽያ ዶርትሙንድ ነጥብ ጥለዋል። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ፣ ቡንደስ ሊጋ እና የፈረንሳይ ሊግ አንድ ዋና ዋና ጉዳዮች በዝግጅታችን ይቃኛሉ።
መሸጋገሪያ
አትሌቲክስ
ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች የተሳተፉባቸውን የሩጫ ውድድሮች ያስተናገደችው የብራሰልስ ከተማ እንደ ወትሮው ወርቁን እንካችሁ አላለችም ። የጃፓኗ ቶክዮ የፊታችን መስከረም ወር በምታስተናግደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ምክንያት በሊጉ ውጤታማ አትሌቶች ባልተሳተፉባቸው ውድድሮች ከፍተኛው ውጤት ሁለተኛ ሆኖ ተመዝግቧል። ሉግዘምበርጋዊ አትሌት ሩበን ኩዌሪንጄን ባሸነፈበት የወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሠናክል ውድድር አትሌት ጌትነት ዋለ 8:09:62 በመግባት ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። ኬንያዊቷ አትሌት አግነስ ጄቤት ንጌትች ባሸነፍችበት የ5ሺ ሜትር የሩጫ ውድድር ደግሞ ልቅና አምባው እና አለሽኝ ባወቀ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነዋል። የፊታችን ረቡዕ እና ሐሙስ ዙሪክ ላይ ፍጻሜውን የሚያገኘው የዓመቱ የዳይመንድ ሊግ ውድድር በሶስት እና አምስት ሺ ሜትር የሩጫ ውድድሮችኩማ ግርማ በ20 ነጥቦች ሲመራ ለባህሬን የሚሮጠው ብርሃኑ በለው እና ዮሚፍ ቀጄልቻ በ19 እና እና 17 ነጥቦች ይከተላሉ ። ኬንያዊው ኤድሙንድ ሴሬም በ24 ነጥብ በሚመራው
የሶስት ሺ መሰናክል ውድድር ሶፍያኔ ኤልባካሊ በ23 ነጥብ ሲከተል ፤ ሳሙኤል ፍሬው በ19 ነጥቦች ሶስተኛ ነው።
በሴቶች አሜሪካዊቷ አዲሰን ዊሌይ በ26 ነጥቦች በምትመራበት የ800 ሜትር ውድድር ጽጌ ዱጉማ በ24 ነጥቦች ትከተላለች። ኬንያዊቷ ብአትሪክ ቼቤት በ32 ነጥቦች አሸናፊነቷን ባረጋገጠችበት የ3000 እና 5000 ሜትር ውድድሮች ጉዳፍ ጸጋይ በ17 ነጥቦች ሁለተኛ ናት ። በ3000 ሜትር መሰናክል ውድድር የመጨረሻ ውድድር ብዙም ውጤት ይቀይራል ተብሎ ባይታሰብም ሲምቦ አለማየሁ ኬንያዊቷ ፋይዝ ቼሮቲችን ተከትላ በ23 ነጥብ ሁለተኛ ናት ። ቼሮቲች ምድቡን በ31 ነጥቦች ትመራለች።
እግር ኳስ
የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አሜሪካ ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ ለሚያስተናግዱት 23ኛው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ከግብጽ ብሔራዊ ቡድን ጋር ቀሪ የማጣሪያ ጨዋታዉን ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛል። በምድብ አንድ ከግብጽ ፤ ቡርኪና ፋሶ ፣ ሴራሊዮን ፣ ጊኒ ቢሳኦ እና ጂቡቲ ጋር የተደለደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በማጣሪያዉ እስካሁን ባደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች በሰበሰባቸው ስድስት ነጥቦች አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቡድኑ በቀሪ መርሃ ግብሮቹ ከፍርዖኖቹ ጋር በካይሮ የሚደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ግብጽ ከኮሮና ክልከላ ወዲህ ለዚህ ጫወታ ከ50 ሺ በላይ ተመልካቾች ስታድየም ገብተው እንዲመለከቱ መፍቀዷ ተሰምቷል። በዚህ ከስፖርታዊ ውድድር ባሻገር የህዳሴ ግድብ በሚመረቅበት ወቅት ለሚደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ምን ይመስላል ስንል የአዲስ አበባ ተባባሪ ዘጋቢያችን ኦምና ታደሰን በስልክ አነጋግረናል።
ቡንደስ ሊጋ
የጀርመን ቡንደስሊጋ ከሌሎች የአውሮጳ ዋና ዋና ሊጎች አንድ ሳምንት ዘግይቶ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ውድድሮቹን በይፋ ጀምሯል። በመክፈቻው ዕለት ባለፈው ዓርብ በሜዳው አር ቢ ላይፕሲችን ያስተናገደው የአምናው ሻምፒዮን ባየር ሙንሽን ግማሽ ደርዘን ጎሎች በማስቆጠር ዓመቱን ከፍ ባለ ድል ጀምሯል። በውድድር ዓመቱ የጎል አነፍናፊው ሊዊዝ ዲያዝን ከሊቨርፑል ያስፈረመው ሙንሽን በአስፈሪ የፊት መስመር መከሰቱን አሳይቷል። በጫወታው እንግሊዛዊው የጎል አዳን ሃሪ ኬን ሃትሪክ በመስራት ገና ከወዲሁ ከፍተኛ የጎል አስቆጣሪነቱን መምራት ጀምሯል። ቀሪዎቹን 2 ጎሎች ማይክል ኦሊሴ እንዲሁም ቡድኑን አዲስ የተቀላቀው ሊዊስ ዲያዝ አስቆጥረዋል። በውድድሩ ሴይንት ፓውልን ከሜዳዉ ውጭ የገጠመው ዶርትሙንድ 3 አቻ አጠናቆ ነጥብ ጥሎ ለመመለስ ተገዷል። አምና በሊጉ ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ባየር ሊፈርኩሰን በሜዳው በሆፈንሃይም 2 ለ 1 ተሸንፏል። አምና የሊጉ ብርቱ ተፎካካሪ የነበረው አይንትራ ፍራንክፈርትም እንደ ሙንሽን ሁሉ በሜዳው ወርደርን ? ገጥሞ በሰፊ የጎል ልዩነት 4 ለ 1 አሸንፏል። ሊጉ በጀመረበት የመጀመሪያው ሳምንት የዶርትሙንድ እና ማየንዝ ተጫዋቾችን በቀይ ካርድ ከሜዳ አሰናብቷል።
ፕሪምየር ሊግ
በሁለተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከተስተናገዱ ዋና ሁነቶች ውስጥ የሊጉን ሰንጠረዥ መምራት የጀመረው አርሴናል አሁንም የተጫዋቾች ጉዳት እንዳጠላበት የተመለከተው መረጃ ቀዳሚ ነው። ባለፈው ቅዳሜ ከአዳጊው የሊድስ ዩናይትድ ጋር በኤሜሬትስ ጫወታውን ያደረገው አርሴናል ሁለት ወሳኝ ተጫዋቾቹን በጉዳት ለመቀየር መገደዱn ይታወሳል። አምበሉ ማርቲን ኦዴጋርድ እና አጥቂው ቡካዮ ሳካ በደረሰባቸው የትከሻ እና የጡንቻ መሳ,ሳብ ጉዳት ከሜዳ ከወጡ በኋላ ምን ያህል ከሜዳ ይርቃሉ የሚለው መረጃ ተጠባቂ ነበር ። ዛሬ ከወደ ሰሜን ለንደን የተss,ማው መረጃ እንደሚያመለክተው አምበሉ ማርቲን ኤዴጋርድ በቅርቡ ወደ ጨዋታ መመለስ እንደሚችል ሲነገር ቡካዮ ሳካ ግን በትንሹ ለአራት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ታውቋል። ሳካ ባለፈው ዓመት በደረሰበት ተሳሳይ ጉዳት ለሶስት ወራት ከሜዳ ርቆ እንደነበር ይታወሳል። አ,ርሴናል በዕለቱ አዲስ ፈራሚው ቲምበር እና ዮጎሬሽ ሁለት ሁለት ጎሎች እንዲሁም በጉዳት ተቀይሮ የወጣው ሳካ አንድ ጎል በድምሩ አምስት ለዜሮ በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።
በሌላ የሊጉ ጨዋታ ዛሬ ምሽት በሊቨርፑል እና ኒውካስትል መካከል የሚደረገው የሁለተኛ ሳምንት ጫወታ በእጅጉ ተጠባቂ ነው። የኒውካስሉን አጥቂ አሌክሳንደር ኢሳክን ለማስፈረም ሊቨርፑል ብርu ፍላጎት ማሳየቱ እና አጥቂው ኢሳቅ ከክለቡ አመራሮች ጋር እስጣገባ ውስጥ እስከመግባት ያደረሰው ቀያዮቹን የመቀላቀል ፍላጎት ሳይቋጭ ክለቦቹ መገናኘታቸው ጫወታው እንዲጠበቅ አድርጎታል። የመጀመሪያ ሳምንት ጫወታቸውን ሊቨርፑል በሜዳው በርንማውዝን 4 ለ 2 ሲያሸንፍ ኒውካስትል ከሜዳው ውጭ ከአስቶን ቪላ ጋር ነጥብ ተጋርቶ ተመልሷል። ሊቨርፑል ከዛሬ ጫወታ በተጨማሪ የፊታችን እሁድ ከአርሴናል ጋር በአምፊልድ የሚad,ርገው ግጥሚያ የእግር ካስ አፍቃሪያን ገና ከወዲሁ የሚጠብቁት ጨዋታ ሆኗል።
ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ሴይንት ጀምስ ፓርክ በሚያስተናግደው የሁለቱ ክለቦች ጫወታ ለሁለቱም ወሳን አንድምታ እንዳለው ተመልክቷል።
በሊጉ ትናንት እሁድ በተደረጉ ጫወታዎች በጫና ውስጥ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድ በክራቨን ካቴጅ ፉልሃምን ገጥሞ ነጥብ ተጋርቶ ተመልሷል። በክረምት የዝውውር ወቅት ወሳኝ ጨዋታዎችን ማስፈረም የቻለው ዩናይትድ ባለፈው ሳምንት ከአርሴናል ጋር የነበረው ድንቅ አጨዋወት መድገም አለመቻሉ አግራሞት ከማጫሩም በላይ አሁንም ሁነኛ ጎል አስቆጣሪ አለማግኘቱ ማሳያ ሆኗል። ዩናይትድ በሁለት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ይዞ አስራ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ላሊጋ
በስፔይን ላሊጋ ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና ተከታታይ ጨዋታዎቻቸውን ማሸነፍ የቻሉበትን ዉጤት ሲያስመዘግቡ ቪያሪያል ከደረጃው ሰንጠረዥ አናት ያስቀመጠውን የ5 ለ 0 ድል ዢሮና ላይ መቀዳጀቱን ተመልክተናል። የአምናው ሻምፒዮን ባርሴሎና ከ2 ለ,0 መመራት አንስቶ ዉጤቱን ወደ 3 ለ 2 መቀልበስ ሲችል በዓመቱ በሊጉ ብርቱ የፍክክር ጊዜ እንደሚኖር ገና ከወዲሁ አሳይቷል።
በፈረንሳይ ሊግ አንድ ሊዮን ሜትስን 3 ለ0 አሸንፎ ሊጉን በጎል ልዩነት መምራት ሲችል ፤ ፔዤም በሜዳው አንገርስን አስተናግዶ በጠባብ የጎል መጠን 1 ለ 0 አሸንፏል። በሊጉ ሎሪየንት ሬኔስን ያሸነፈበት የ 4 ለ 0 ዉጤት በርካታ ጎል የተቆጠረበት ሆኖ ተመዝግቧል።
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ