የሚያዝያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም፤ የስፖርት ዝግጅት
ሰኞ፣ ሚያዝያ 13 2017አትሌቲክስ
በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የአለም ክፍሎች በተካሄዱ የጎዳና ላይ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሽናፊ ሆነዋል። በቦስተን የ5 ኪሎሜትር ውድድር አትሌት ገላ ሀምበሴ 14 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ በመግባት በአንደኝነት አሸናፊ ስትሆን። በቻናይ በተደርገ የግማሽ ማራቶን ውድድር ደግሞ አትሌት ፈታ ዘርአይ ቀዳሚ ሆና በመግባት ድል አድትርጋለች። አትሌት ፈታ ቻይና የተደርገውን የግማሽ ማራቶን ውድድር ለማጠናቀቅ 1ሰዓት ከ06 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ የፈጅባት ሲሆን አትሌትዋ የገባችበት ሰአት የቦታውን ክብረወሰን ያሻሻለ እንደሆነ ተንግርዋል።
በተመሳሳይ የአትሌቲክስ ዜና በሀርቺንዶ ማራቶን በሴቶቹ አትሌት ብዙአለም ጨቅሌ 2 ሰዓት ከ30ደቂቃ በመግባት ስታሽንፍ አትሌት ፀሐይ ገብሬ ደግሞ በስድስት ሰከንድ ተቀድማ ሁለተኛ ወጥታለች።በወንዶቹ አትሌት ሞላልኝ ፋንታሁን 2 ሰዓት ከ12 ደቂቃ ከ39 ሰከንድ ውድድሩን በማጠናቀቅ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
የለንደን ማራቶን
የፊታችን እሁድ የሚካሄደው የለንደን ማራቶን በኮከብ አትሌቶች የታጀበ የልሂቃን የውድድር ሜዳ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። በሴቶች ውድድር ትግስት አሰፋ እና ሲፋን ሀሰን በወንዶች ደግሞ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ እና ቀነኒሳ በቀለ ውድድሩን ውበት ከሚያላብሱት ምርጥ ሯጮች መካከል ናቸው ሲባል ሰንብቶዋል። ሆኖም የዓለም ክብረ-ወሰን ባለቤት ሩት ቼፕንጌቲች ከአምናው ሻምፒዮን ፔሬስ ጄፕቺርቺር ጋር በለንደን ማራቶን ውድድሩን አልሳተፍም ስትል ማስታወቅዋ ትላንት ተሰምቷል ።
ባለፈው አመት በተካሄደው የለንደን ማራቶን ሪከርድ በሆነ ጊዜ ሁለት ሰአት ከ16 ደቂቃ ከ16 ሰከንድ ያሸነፈው ኬንያዊው ጄፕቺርቺር በቁርጭምጭሚት ጉዳት ከውድድሩ ውጪ መሆኑ ታውቆዋል ።
ሁለቱ የኬንያውያን ፈርጦች የሌሉበት ውድድር የአገራቸው ልጅ ቪቪያን ቼሩዮት የንግስናውን ቦታ እንድምትወስድ አስቀድሞ ተገምቷዋል ። የ41 ዓመቷ ቼሩዮት የለንደን ማራቶንን በ2018 አሽናፊ ነበረች ሲሆን ከኢትዮጵያውያን አትሌቶች ቀላል የማይባል ፉክክር እንደሚጠብቃት ተገምቷዋል ።
እግር ኳስ፤ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ
የ2017 የ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 26 ኛ ሳምት ጨዋታ በሀዋሳ ዪንቨርስቲ ስታድየም በመካሄድ ላይ ነው ። ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ የተደርጉት ሁለት ጨዋታዎች ሁለቱም በተመሳሳይ 3 ለ 1 በሆነ አሽናፊነት ተጠናቀዋል። ሀዲያ ሆሳእና ወላይታ ድቻን 3 ለ 1፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ ዓዲግራት በተመሳይ 3 ለ 1 አሸንፏል ።ትላንት እሁድ ኢትዮጵያ ቡና - ሲዳማ ቡናን 1 ለ0 ሲያሽንፍ አርባ ምንጭ ከተማ እና ስሑል ሽረ 0ለ0 ተለያይተው ነጥብ ተጋርተዋል።
የ26ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ እና ነገ በሚካሄዱ 5 ጨዋታዎች የሚካሄድ ዛሬ መቻል ከአዳማ ከተማ፤ ፋሲል ከነማ - ከ ድሬዳዋ ከተማ እና ባህር ዳር ከተማ - መቐለ 70 እንደርታ፤ ነገ ማክሰኞ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ፕሪምየር ሊጉን ከሚመራው ኢትዮጵያ መድን ፣ ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር እንደሚጫወቱ የውጣው መረሀ ግብር ያሳያል ።
ዛሬ እና ነገ ሚደረጉትን ጨዋታዎች ሳይጨምር እስካሁን በተካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር የኢትዮጵያ መድን በ 48 ነጥብ ሲመራ የኢትዮጵያ ቡና በ 39 ነጥብ ይከተላል። ባህርዳር ከተማ እና ፣ወላይታ ዲቻ ፣ በ 37 ነጥብ በጎል ክፍያ ተለያይተው ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ ። ሃዋሳ ከተማ፣ አዳማ ከተማ፣ ስሑል ሽረ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከ15ኛ እስከ 18ኛ ደረጃን በመያዝ በፕሪምየር ሊጉ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙ ቡድኖች ሆነዋል ።
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ
ትላንት በንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከተደረጉት ጨዋታዎች መካከል ሊቨርፑል በወራጅ ቀጠና ያለውን ሌስተር ሲቲ ያሸነፈበት በኪንግ ፓወር ስታዲየም የማዕዘን ባንዲራ ላይ የተሰቀለው ቀይ ማሊያ፣ የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ለማግኘቱ ማሳያ ሆንዋል። ትላንት አሌክሳንደር- አርኖልድ በ 76 ኛው ደቂቃ ከመረብ ባሳረፈው ጎል ሊቨርፑል 3 ነጥብ ይዞ ወቷዋል። ቀበሮዎቹ የሊቨርፑል የኋላ መስመርን መሻገር ተስኗቸው ከመታየታቸው ባሻገር በሜዳቸው ባደረጉት ዘጠነኛ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ጎል ሳያስቆጥሩ ወደ ሻንፒዮን የሚመልስ የመጀመሪያው ቡድን ሆንዋል።
የዛሬን አያድርገው እና በ 2015/16 እና 2018/19 የፐሪምየር ሊጉን ዋንጫ አንስተው የነበሩት ሌስተሮች ትላንት በ76ኛ ደቂቃ በአሌክስ አርኖልድ በተቆጠርባቸው ጎል ተሽንፈው ከሜዳ ብቻ ሳይሆን ከ ዘንድሮው ፕሪምየር ሊጉ አስቀድመው መሽኝታቸውን ያረጋገጡ ቡድኖች ሆነዋል።
ኢትዮጵያ በናንጂንግ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ተጨማሪ ሜዳሊያዎች አሸነፈች
በአንፃሩ ሊቭርፑል በወራጅ ቀጠናው ሲዳክር የሰነበተውን ሌስተር ሲቲ ያሸነፉበት ጨዋታ አስልጣኝ አርኒስሎት የወደፊት እጣ ላይ ይነሱ የነበሩት ጥያቄዎችን ሁሉ ወሬ ሆነው እንዲሰነብቱ ያደረገ ይመስላል። በግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አጉዋጊ ከነበሩት ጨዋታዎች መካከል ሌላው ቼልሲ ከፉልሀም ጋር አድርጎት የነበርው ጨዋታ ነው ።አንድም ቸልሲ እያደር ከሚዳው ውጭ ማሽነፍ ተራራ ሆኖበት ስለሰነበተ ሁለትም በሻንቶፒንስ ሊጉ ለመሰንበት ይህን ጨዋታ ማሽነፍ ወሳኝ ስለነበር ፣
ሰማያዊዎቹ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን የቻምፒየንስ ሊግ እግር ኳስ ያላቸውን ተስፋ ከፍ እንዲያደርጉ አስችሎዋል። በሜዳቸው የተጫወቱት ፉልሀሞች በ 1 ለ 0 መሪነት ጨዋ ከአንድ ሰአት በላይ ይዘው ቢቆይም ተቀይሮ የገባው የ19 አመቱ ጆርጅ የመጀመሪያውን ጎል በ 83ኛው ደቂቃ ፤ላይ አስቆጥሮ ቡድኑን አቻ አደረገ መደብኛው የጨዋታ ግዜ ተጠናቆ በተጨማሪ ሰአት 93 ኛ ደቂቃ ላይ ፔድሮ ኔቶ ሁለተኛውን ጎል በማስቆጠርሩ ቸልሲ በ 2 ለ 1 አሽናፊነት 3 ነጥብ ይዞ ከሚዳ እንዲወጣ ከማስቻሉም በላይ በ ፕሪምየር ሊጉ 4 ኛ ደረጃ ላይ እንዲገን አድርጎታል ።
አርሰናል ኢስዊችን በሰፊ የጎል ልዪነት ያሽነፈበት ጨዋታ ሲጠበቅ የነበረው በደጋፊዎቹ ብቻ ሳይሆን በቀያዪቹም ነበር። በፖርትማን ሮድ 10 ተጫዋቾችን ይዞ ኢፕስዊች በምቾት ያሽነፉት የመድፈኞቹ ድል ሊቨርፑልን የፕሪምየር ሊግን ዋንጫን አስቀድሞ ማሽነፉን የሚያርጋግጥበትን እድል ከልክሏል። መድፈኞቹ ለቻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ከሪያል ማድሪድ ጋር ከተገናኙ በኋላ ባደረጉት የመጀመሪያ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ በኢፕስዊች ቡድን ላይ ሌላ ግሩም ብቃት አሳይተዋል። አርሰናል በ14ኛ በሊአንድሮ ትሮሳርድ በ 28 ኛ ው ደቂቃ ገብርኤል ማርቲኔሊ ሁለተኛውን ጎል ከመረብ አሳረፈ በ32ኛው ደቂቃ ሌፍ ዴቪስ በሳካ ላይ ባሳየው የማይገባ ጥፋት ቀይ ካርድ ማግኘቱ የአይፕስዊች ስራ የበለጠ ከባድ አድረገው።
ትሮሳርድ በ69ኛው ደቂቃ ላይ የጨዋታውን ሶስተኛ የራሱን ሁለተኛ ጎል አስመዘገበ ።ለአርሰናል ተቀይሮ የገባው ኤታን ንዋኔሪ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሁለት ደቂቃዎች ብቻ ሲቀሩት አራተኛውን ጎል አስቆጥረ በጨዋታው ብዙ የጎል እድሎች የነበሯቸው መድፈኞቹ 4 ል0 በሆነ ሰፊ ድል አሽንፊ ሆኑ በዚህ በ2025 የፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ግዜ አይፕስዊቾች በሚዳቸው ተሽንፈው ነጥብ ጥለው ሲወጡ ይህ ሰባተኛው ሽንፈታቸው ነው
በተቀሩት የግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዘንድሮ ሽንፈት ብርቅ ያልሆነበት ማንችስተር ዪናይትድ በዎልቨር ሀምቶንን 1 ለ0 ሲረታ ቅዳሜ ብረንት ፈርድ ብራይቶንን 4ለ2 ኤቨርተን በ ማንችስተር ሲቲ 2ለ0 ተረትዋል ዊስትሀም ዮናይትድ ከ ሳውዝ ሀምፕቶን 1፤እ1 ክርስታል ፓላስ ከ ቦርንማውዝ 0ለ0 ተላያይተው ነጥብ ተጋርተዋል አስቶን ቪላ ኒው ካስል ዩናይትድን 4ለ 1 ረትዋል ።
ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዲሱ ፕሬዚደንት ምን ይጠበቃል? አንድ ለአንድ፥ ቃለ መጠይቅ
33 ኛ ሳምንቱን በያዘው የእግሊዝ ፕሪምየርን የደርጃ ሰንጠትዥ ሊቨርፕል በ 79 ነጭብ ሲመራው አርሰናል 13 ነጥብ ልዩነት በ 66 ነጥብ ሁለተኛ ነው ኒውካስል ዩናይትድ በ 59 ነጥብ ሶስተኛ ብዙም ሳይርቅ ማንችስተር ሲቲ በ 58 4 ኛ ሆኖ ይከተላል ቸልሲ ዛሪ ማምሻወን ተስተካካይ ጨዋታውን ከቶትነሀም ጋር ከሚያደርገው ነቲንግሀም ፎረስት ጋር በኩል ነጥብ 5ኛ እና 6 ሆነው በ 57 ነጥብ ይጠባበቃሉ
ነኪንግሀም ፎረስት በለስ ቀንቶት ዛሪ ተጋጣሚውን ካሽነፍ በፕሪምየር ሊጉ 3ኛ ደረጃላይ ተቀመጭ ይሆናሉ ኢፕስዊች ሌስተር ሲቲ እና ሳውዝ ሀምፕቶን እንደ ቅደም ተከተላቸው በ 21 18 እና በ11 ነጥብ የዘንድሮው የፕርምየር ሊጉን ተሰናባች ቡድን መንደር ይዘዋል ።
የጀርመን ቡንዲስ ሊጋ
ትላንት በተካሄደው የጀርመን ቡንድስሊጋ ጨዋታ ኦገስበርግ ፍራንክፈርት ባዶ ለ ባዶ ተለያይቶ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል። በሲግናል ኢዱና ፓርክ ከ80 ሺህ በላይ ደጋፊዎቸ የተከታተሉት የቦሩሲያ ዶርትሙንድ እና ቦሩሲያ ምሽንግላድባች ጨዋታ በ ቦሩሲያ ዶርቱመንድ 3ለ2 አሽናፊነት ተጠናቅዋል ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ሶስቱም ጎሎች በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ የትቆጠሩ ሲሆኑ ከረፍት መልስ ከመረብ የትገናነው የ ምሸን ግላድባች ሁለተኛዋ ጎል ብቻ ነበር ።ሴንት ፓውሊ እና ባየር ሊቨርኩሰን 1ለ 1 ተለያይተዋል
የአፍሪቃ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና የአውሮጳ ዋንጫ አንድምታዎች
ቅዳሜ ፍሪቡርግ ሆፈንሃይም 3 ለ 2 ሲረታ ሃይደንሃይም በ ባየር ሙኒክ 4 ለ 0 በሚዳው ተሽነፎዋል ሜይንዝ 05 ከ ቮልፍስቡርግ 2ለ 2 ሊይፕዚግ ከ ሆልስታይን ኪኤል 1ለ 1 ዩኒየን በርሊን ከ ስቱትጋርት 4 ለ4 ተለያይተው ተለያይቶ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቶዋል ቨርደር ብሬመን ቦኩም 1ለ 0 ረቷል።
30ኛሳምንቱን በያዘው የጀርመን ቡንድስ ሊጋ ባየር ሙኒሽ በ 8 ነጥብ የበላይነት 64 ነጥብ ቡንዲስ ሊጋውን ሲመራው ባየር ሊቨርኩሰን በ 64 ነጥብ ሁለተኛ ሆኖ ይከተላል ፍራንክፈርት በ 52 ነጥብ ሶስተኛ ሊፕዚንግ በ 3 ነጥብ ተበጦ በ 49 ነጥብ 4ኛ ነው ፍራይቦርግ እና ሜይንዝ 05 በ 49 እና በ48 ነጥብ 5ኛ እና 6 ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ የ ወራጅ ቀጠናውን ሃይደንሃይም በ22 ነጥብ ቦኩም በ20 ነጥብ ሆልስታይን በ 19 ነጥብ ይዘውታል።
የሜዳ ትኒስ ውድድር
በ ስፔን ባርሲሎና ኦፕን የሚዳ ትንንስ ውድድር ሆልገር ሩኔ ዋንጫ ባለቤት የሆነውን ካርሎስ አልካራዝን ጋር ባደረገው ጨዋታ አስደናቂ ብቃት አሳይቷል።
የዴንማርክ ሩኔ ከስፔናዊው ካርሎስ ጋር የነበረውንጨዋት 7-6 (8-6) 6-2 አሸንፏል።
ከሁለት አመት በሁዋላ በሩኔ የታየው የጨዋታ ብቃት ከፍተኛ አድናቆትን አስችሮታል ።
በአራት አመታት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ የባርሴሎና ሻምፒዮንነት የተካፈለው አልካራዝ በሁለተኛው ዙር ያገኛቸውን አራቱን የእረፍት እድሎች ሳይጠቀምበት የቀረ ከምሆኑም ባሻገር የህክምና እረፍት ቢወስድም የተወረወረበትን ጠንካራ የሩኔን ኩዋስች መመከት ሳይችል ቀርቶ ድል ሆኗል ።
በተመሳሳይ በሴቶች በተካሄደ የሜዳ ቴንስ ውድድር የአለም ቁጥር አንደ የሜዲስ ቴንስ ተጫዋች የሆነችው አሪና ሳባሌንካ ጣሊያናዊቷ ጃስሚን ፓኦሊኒ 7-5 6-4 በማሸነፍ አራተኛ ግዜ ለስቱትጋርት ኦፕን የፍጻሜ ውድድር ደርሳለች።
ሃና ደምሴ
ነጋሽ መሐመድ