ሉሲ እና ሰላም ፕራግ ውስጥ ለእይታ የመቅረባቸው አንድምታ
ዓርብ፣ ነሐሴ 23 2017ማስታወቂያ
ድንቅነሽ ወይም ሉሲ እና ሰላም ቅሪተ አካላት ቼክ ሪፐብሊክ ፕራግ ውስጥ ለእይታ በቅተዋል። ኤግዚቢሽኑን በተመለከተ የባህል ሚንስትሯ ሰላማዊት ካሳ በይፋዊ የማህበራዊ መገናኛ ገጻቸው የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት ለመንገር፤ አዲሲቷን ኢትዮጵያንም ለአለም ለማብሰር ድንቅነሽ/ሉሲ እና ሰላም በማዕከላዊ አውሮፓ ተገኝተዋል» በማለት ጽፈዋል።
በኤግዚብሽኑ ላይ ካገኙት አንጋፋው ተመራማሪ ፕሮፌሰር ዶናልድ ጆሃንሰን እና ሰላምን ያገኙት እውቁ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ አለምሰገድ ተገኝተዋል።
የሰው ልጅ አመጣጥን የሚያሳየውን ኤግዚቢሽን ለማካሄድ ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጋቸውን የቼክ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ፒተር ፊያላ ተናግረዋል።
የድንቅነሽ ወይም ሉሲ እና ሰላምቅርተ አካላት በፕራግ ለሁለት ወራት ያህል ለህዝብ እይታ ክፍት ይሆናሉ ነው የተባለው። ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ተጨማሪ ረዥም ዘመናት ያስቆጠሩ ቅሪተ አካላት መገኘታቸው ሀገሪቱ አሁንም ለቅድመ የሰው ልጅ አመጣጥ ጥናት መሰረት የጣሉ ግኝቶች መሆናቸው ተነግሯል።
አዜብ ታደሰ
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ